Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባዋ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም ብለዋል።

ከንቲባዋ በመግለጫቸው የከተማ አስተዳደሩ በየሦስት ወሩ የሚታደስ መመሪያ እንደነበረው አስታውሰዋል።

በከተማዋ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በመኖሩ በዜጎች ላይ ጫና እያስከተለ በመሆኑ የቤት ኪራይ መጨመር መከልከሉን አስረድተዋል።

በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ አይቶ ደንቡ እስካልተሻሻለ ድረስ ምንም አይነተ የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አከራዮችም ሆኑ ተከራዮች ይህንኑ ማወቅ እንዳለባቸው ጠቁመው ክልከላውን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ዙሪያ ዜጎች መብትና ግዴታቸውን በቅጡ ተገንዝበው እንዲሰሩም አስገንዝበዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.