Fana: At a Speed of Life!

የቡድን 20 እና “የጋራ ብልጽግና” የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡድን 20 እና የጋራ ብልጽግና ቡድን አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባዎች ዛሬ በኢንዶኔዥያ ባሊ ግዛት እና በታጂኪስታን መዲና ዱሻንቤ ተጀምሯል።

በዛሬው የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ አሜሪካ ዩክሬን ላይ በሩስያ “የተፈጸመውን ወረራ” በዋና አጀንዳነት በማንሳት የዓለም ኢኮኖሚ ኃያላን የሁኑት ሀገራት በሩሲያ ላይ ጫና እንዲያሳድሩ ግፊት ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከቻይና አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር “በታይዋን እና በቻይና መካከል የሰፈነውን ውጥረት” ለማርገብ የጎንዮሽ ውይይት ያካሂዳሉ ተብሏል፡፡

የቡድን 20 የተባለው ስብስብ የተመሰረተው በፈረንጆቹ 1999 ሲሆን፥ ዓላማውም የዓለም አቀፉ ፋይናንስ እንዲረጋጋ እና የአየር ንብረት ለውጥ እንዳይባባስ ለማድረግ እንዲሁም በዘላቂ ልማት እና በዓለም ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመምከርና ለመወሰን ነው።

በተመሳሳይ የጋራ ብልጽግና አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ በታጂኪስታን መዲና ዱሻንቤ እየተካሄደ ሲሆን፥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በዓለም አቀፍ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ይለዋወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ሲጂቲ ኤን ዘግቧል።

የቡድን 20 አባል ሀገራት አርጀንቲና፣ አውስትራሊያ፣ ብራዚል፣ ካናዳ፣ ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሕንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ኢጣሊያ፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ሜክሲኮ፣ ሩሲያ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቱርክ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ እና አውሮፓ ኅብረት ናቸው፡፡

የጋራ ብልጽግና አባል ሀገራት ደግሞ የቀድሞ የብሪታኒያ ቅኝ ግዛት የነበሩ 56 ሀገራት መሆናቸውም ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.