Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን መሀል ሜዳ ከተማ በቦምብ ጥቃት የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን መሀል ሜዳ ከተማ በአንድ ግለሰብ በተወረወረ ቦምብ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፋን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ ፓሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጥላሁን ደበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ድርጊቱ ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት አካባቢ በከተማዋ 03 ቀበሌ በሚገኝ አንድ መጠጥ ቤት ነው የተፈጸመው።

በተፈጸመው የቦምብ ጥቃትም የሶስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ ሶስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ደብረ ብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል ተልከው ህክም እየተደረገላቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።

ግለሰቡ ከፈጸመው የቦንብ ጥቃት በተጨማሪ በሽጉጥና በጩቤ 13 ሰዎችን ማቁሰሉ ተነግሯል።

ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ጥላሁን ደበበ ተናግረዋል።

በአበበ የሸዋልዑል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.