Fana: At a Speed of Life!

አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ነገ የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ እንድትመራ ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ምሽት የሚከናወነውን ወሳኝ ጨዋታ እንድትመራ ተመርጣለች።
የ2022 የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
12 ሀገራት በሦስት ምድብ ተከፋፍለው የሚያደርጉት ፍልሚያ ከዛሬ ጀምሮ የምድብ የመጨረሻ መርሐ-ግብሮች የሚደረጉበት ሲሆን÷ በምድብ ሁለት በካሜሩን እና ታንዛኒያ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ አርቢትር በዋና ዳኝነት እንደምትመራው ታውቋል።
ነገ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በካዛብላንካ ኮምፕሌክስ ሞሀመድ ስታዲየም የሚደረገው ጨዋታ÷ በአንድ ነጥብ ተበላልጠው የምድቡ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ለሆኑት ቱኒዚያ እና ካሜሩን እጅግ ወሳኝ ነው።
ይህንን ተጠባቂ ጨዋታ ሊዲያ ሞሮኳዊቷን ፋቲያ ጄርሞሚ እና ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመጣችው ሚሪሌ ካንጂንጋን ረዳት እንዲሁም የእስዋቲኒ ዜግነት ያላትን ሌቲካ አንቶኔላን አራተኛ ዳኛ አድርጋ እንድትመራ ካፍ ምደባ ማከናወኑን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡
ሊዲያ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ካሜሩን እና ዛምቢያ ያደረጉትን ጨዋታ በአራተኛ ዳኝነት እንድትመራ ተመድባ የነበረ ቢሆንም የጨዋታው ዋና ዳኛ 58ኛው ደቂቃ ላይ ተጎድታ ቀይራት ገብታ ጨዋታውን በመሐል አርቢትርነት በመምራት ጨርሳለች።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.