Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ 1443ኛው የኢድ-አልአድሃ (ዐረፋ) በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ 1443ኛው የኢድ-አልአድሃ (ዐረፋ) በዓል በድምቀት ተከበረ።
በጅማ ከተማ የፈትህ መስጂድ ኢማም ሼህ ሙሀመድ አሚን ተማም በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ሁሉም ሰው ፈጣሪውን ሊፈራና ከመጥፎ ነገሮች ሊከለከል እንዲሁም እውቀትና ጉልበቱን ለመልካም ተግባር ሊያውል ይገባል ብለዋል፡፡
ይህ ዕለት የአላህ መልዕክተኛ ነቢዩ ሙሀመድ ዘረኝነትንና ጎጠኝነትን ያወገዙትበት በመሆኑ፥ ሙስሊሞች አፍራሽ ከሆኑ ተግባራት ሊከለከሉ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ሕዝበ ሙስሊሙ በአሉን ሲያከብር የተቸገሩትን፣ የታመሙትንና አቅመ ደካሞችን ማሰብ እንዳለበት ሸህ ሙሀመድ አሚን ገልጸዋል።
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ነጂብ ራያ፥ ሕዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን በማጠናከር ሀገሩንና እምነቱን ሊጠብቅ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በሙክታር ጣሃ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.