Fana: At a Speed of Life!

በበዓላት ወቅት የሚታየው መተሳሰብና ፍቅር በሁሉም ጊዜያት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል የእስልምና ሃይማኖት አባቶች ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1443ኛው ኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በጋምቤላ ከተማ በድምቀት ተከብሯል፡፡
በሶላት ስነስርዓቱ የሀይማኖት አባቶች እንዳሉት፥ በበዓላት ወቅት የሚታየው መተሳሰብና ፍቅር በሁሉም ጊዜያት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
ሙስሊሙ የኢድ አል አድሀ /አረፋ/ በዓልን አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመጠየቅ እንዲያሳልፍም ጥሪ አቅርበዋል።
ታላቁ የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በፍቅር፣ በአንድነትና በወንድማማችነት እንዲከበር ህዝበ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ አንድነቱንና ወንድማማችነቱን ሊጠብቅ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።
ሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በመረዳዳትና በመተሳሰብ ኢትዮጵያን ከፈተና አውጥተን ወደምናስበው ስኬት ልናደርሳት ይገባል ሲሉ የሀይማኖት አባቶቹ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ እንዲሁም ለሀገር ሠላም እና ልማት ዱዓ በማድረግ በዓሉን እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል።
ሶላቱ ከተከናወነ በኋላ ሌሎች ሃይማኖታዊ ስርዓቶችም መካሄዳቸውን ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.