Fana: At a Speed of Life!

በበጀት አመቱ ለውጭ ገበያ ከቀረበ ቡና 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 12 ወራት ለውጭ ገበያ ከቀረበ የቡና ምርት 1 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን አስታወቁ።

ገቢው ወደ ውጭ ከተላከ 300 ሺህ ቶን የቡና ምርት የተገኘ መሆኑን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በበጀት አመቱ የተገኘው ገቢ በዓመት ይገኝ ከነበረው አማካይ ጋር ሲነጻጸር የ500 ሚሊየን ዶላር ጭማሪ እንዳለውም አመላክተዋል።

ሚኒስትሩ ገቢው እንዲገኝ ላደረጉ የቡና አምራቾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.