Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በተፈጠረው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት በአውሮፕላን በረራዎች ላይ መስተጓጎል መፈጠሩን አየር መንገዱ ገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በተፈጠረው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ከአዲስ አበባ በሚነሱና አዲስ አበባ በሚያርፉ በረራዎች ላይ መዘግየት መፈጠሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው የበረራ መዘግየትና መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ደንበኞችም የተፈጠረውን ችግር ተገንዝበው አየር መንገዱ ስለሁኔታው የሚያቀርበውን መረጃ እንዲከታተሉ መጠየቁን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

አዲስ አበባ ዛሬ በዝናብና ጭጋጋማ አየር ተሸፍናለች።

የከተማዋ የዛሬው የዓየር ሁኔታም ከፍተኛው 16 ዲግሪ ሴልሺየስ ሲሆን፥ ዝቅተኛው 13 ዲግሪ ሴልሺየስ መሆኑን የቢቢሲ የዓየር ትንበያ መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.