Fana: At a Speed of Life!

የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ 50 ልዩ ሀገር አቋራጭ አውቶብሶችን ለኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት ድርጅት አስረከበ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ያመረታቸውን 50 ልዩ ሀገር አቋራጭ አውቶብሶች ለኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት ድርጅት አስረክቧል።

በርክክብ ስነ-ስርአቱ ላይ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

 

ርክክብ ከተደረገባቸው በልዩ ሁኔታ የተመረቱ ዘመናዊ አውቶብሶች ውስጥ አምስቱ ለአካል ጉዳተኞች የሚሆን አሳንሰር የተገጠመላቸው ናቸው ተብሏል፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ÷ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዘመናዊ አሰራር የተከተለ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት አየሰራ ይገኛል፡፡

በዚህም የቴክኖሎጂ መረብ በመጠቀምም የኢትኬት አገልግሎት መስጠት ጀምረናል ነው ያሉት ሚኒስትሯ።

አውቶብሶቹ ከፍተኛ የፈረስ ጉልበት ያላቸውና የ45 ሰዎች መቀመጫ፣ በቂ የሆነ የእቃ መጫኛ ፣ በውስጡም የመጸዳጃ እና የማቀዝቀዣ ክፍል ያላቸው ሲሆኑ ሙሉ በሙሉ አርቴፊሻል ኢንተለጀንት ሲስተም የተገጠመላቸው ቅንጡ መሆናቸው በቁልፍ ርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ርክክብ የተደረገባቸው አውቶብሶች የማህበረሰቡን የትራንስፖርት ችግር በመቅረፍ በኩል ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑም ተመላክቷል ።

በቅድስት ተስፋየ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.