Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ኅብረት አዲስ በጣለው የግብር ታሪፍ ላይ ኬንያ እና ዩጋንዳ ቅሬታቸውን አሰሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ኅብረት አባል ባልሆኑ ሀገራት ላይ የጣለው አዲሱ የግብር ታሪፍ ሥራ ላይ ከዋለ ከሣምንት በኋላ ባልተጠበቀ መልኩ የንግድ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩ ተገለጸ፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ኅብረት ÷ አባል ባልሆኑ ሀገራት ገቢ ሸቀጦች ላይ የጣለውን ግብር ወደ 35 በመቶ ማሳደጉን ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል፡፡

የግብር ጭማሬውን ተከትሎ ኬንያ እና ዩጋንዳ በምናስገባቸው የመሠረታዊ አቅርቦቶች እና ሸቀጦች ላይ የዋጋ መወደድ አጋጥሞናል በሚል ለምሥራቅ አፍሪካው ንግድ ምክር ቤት ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ኅብረቱ በበኩሉ ÷ ከአባል ሀገራቱ ውጪ ከሆኑ ሀገራት በሚገቡ ሸቀጦች ላይ ግብር የጨመርኩት የአባል ሀገራቱን አምራቾች ለማበረታታት እና ከቀጠናው ውጭ ከሚገቡ ተመሳሳይ ምርቶች ውድድር ለመከላከል መሆኑን ሊታሰብበት ይገባል ብሏል፡፡

የግብር ጭማሬው የቀጠናውን የኢንዱስትሪ ምርቶች በ0 ነጥብ 04 በመቶ እንደሚያሳድግ እና ወደ 12 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ እንደሚያስገኝ ያመላከተ ሲሆን ከግብር የሚሰበሰበው ገቢ ደግሞ በ5 ነጥብ 5 በመቶ ይጨምራል ብሏል፡፡

በዚህም ለ6 ሺህ 781 ተጨማሪ የቀጠናው ማኅበረሰብ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ነው ኅብረቱ ያመላከተው፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ የሚባሉት 7 ሀገራት ሲሆኑ እነሱም ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ብሩንዲ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ ናቸው ፤ ዋና መሥሪያ ቤታቸው የሚገኘውም በታንዛኒያ አሩሻ ነው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.