Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ የአምስት ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ በኢትዮጵያ ሀገሮቻቸውን ለመወከል ተሹመዉ ከመጡ አምስት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ፡፡

የሹመት ደብዳቤ ያቀረቡት አምባሳደሮችም÷

አምባሳደር ፓሃላ ራላጅ ሳናታና ሱጂሽዋራ ጉናራትና ከስሪ ላንካ ፣

አምባሳደር ኤልሃምዲ ሳላ ፍራንሲስ ከአልጄሪያ፣

አምባሳደር አንቷን ካሚሌሪ ከቫቲካን፣

አምባሳደር ኔስትሮ አሌሃንድሮ ሮዛ ናቫፖ ከኡራጋይ፣

አምባሳደር ሲም ቶንግ ጉክ ከሰሜን ኮሪያ ናቸው።

ፕሬዚዳንቷ በኢትዮጵያ እና በእነዚህ ሀገራት መካከል ያለዉን ግንኙነት ለማጠንከር አምባሳደሮቹ እንዲሰሩ በማበረታት መልካም የስራ ዘመንም መመኘታቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.