Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከቡርኪናፋሶ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከቡርኪናፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦሊቪያ ሩምባ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ ደመቀ ፥ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የረጅም ጊዜ ግንኙነት ከቅኝ ግዛት ዘመን ጀምሮ የተጀመረ መሆኑን ገልፀው፤ በቀጣይ ግንኙነቶች ሊታደስ ይገባል ብለዋል።

በባለብዙ ወገን መድረኮች ስለ ኢትዮጵያ ወሳኝ ጉዳዮችን በተመለከተ የቡርኪናፋሶን ወጥ እና ሚዛናዊ አቋምም አድንቀዋል።

አቶ ደመቀ ፥ ሁለቱ ሀገራት በአቅም ግንባታ ላይ ብዙ ያልተነኩ እምቅ አቅም ያላቸው በመሆኑ ወደ ላቀ ግንኙነት መንገድ የሚጠርግ መሆን አለበት ብለዋል።

ኦሊቪያ ሩዋምባ በበኩላቸው ፥ ኢትዮጵያ የቡርኪናፋሶ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ማዕከል ሆና መቆየቷን አውስተው÷ አስፈላጊነቷም ከመልክዓ ምድራዊ ስፋቷ በላይ ነው ብለዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካ ኩራት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ ÷ የግድቡ መገንባት የውስጥ ሃብቶችን በመጠቀም ለአፍሪካ የዕድገት ምሳሌ እንደሚሆን መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.