Fana: At a Speed of Life!

ኤርትራ እና ሶማሊያ ሁሉን አቀፍ የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤርትራ እና ሶማሊያ በኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና በቀጠናዊ የደኅንነት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመሥራት ሁሉን አቀፍ የጋራ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን ገለጹ፡፡

በሶማሊያ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎችን መዋጋት ለሶማሊያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ዘላቂ ሠላም ፣ መረጋጋት እና ደኅንነት ጭምር ወሳኝ ስለመሆኑ ሀገራቱ ዕውቅና መስጠታቸውን የመግባቢያ ሠነዱ አመላክቷል፡፡

የመግባቢያ ሠነዱን የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው አቻቸው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሁሙድ ፈርመዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ ትሥሥር እና ብልፅግና ዕውን ይሆን ዘንድ የሶማሊያ ሰላምና ዕድገት እጅግ ወሳኝ መሆኑን ሀገራቱ መስማማታቸውንም ሠነዱ ጠቁሟል፡፡

ኤርትራ እና ሶማሊያ ዳያስፖራ ማኅበረሰቦቻቸውን ጨምሮ የሀገራቱ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲጎለብት እንደሚሰሩ ገልጸው ፥ የሀገራቱን ብሔራዊ ጥቅም ያማከለ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።
የሀገራቱን ብሔራዊ ጥቅም ያማከለ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ በውሃ ፣ በግብርና፣ በዓሣ ሐብት ፣ በጤና እና ትምህርት ላይም ትኩረት ያደረገ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ትብብራቸውን ለማስፋት ሀገራቱ መሥማማታቸውንም ነው የመግባቢያ ሰነዱ ያመላከተው።

በሀገራቱ መካከል የባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ስፖርታዊ ሁነቶች እንዲሁም ሣይንስ እና ቴክኖሎጂያዊ ትብብሮች እንዲጎለብቱም ለመሥራት ሀገራቱ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

በአካባቢ ጥበቃ ብሎም የሚከሰቱ ተላላፊ ወረርሽኞችን በጋራ ለመከላካል እና የተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች ላይ በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውም ተገልጿል።

ሁለቱ ሀገሮች በአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ ትሥሥር ለመፍጠርና ወዳጅነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሠሩም ነው በኤርትራ አስመራ በተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነዳቸው ያመላከቱት።

ሰላምን፣ መረጋጋትና ደኅንነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥም በመከላከያ ኃይል እና ደኅንነት ላይ በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውንም በኢትዮጵያ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.