Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኢሳያስ ጅራ ከካፍ ፕሬዚዳንት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞሴፔ በፌዴሬሽኑ ባለቤትነት ግልጋሎት እየሰጠ የሚገኘውን የካፍ የልህቀት ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ የማዕከሉን የተለያዩ ክፍሎች፥ የልምምድ ሜዳ እና የፌዴሬሽኑን “መለስተኛ ትጥቅ ማምረቻ” ተመልክተዋል።

የካፍ ፕሬዚዳንት ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው ፌዴሬሽኑ ያስታወቀው።

ፓትሪስ ሞትሴፔ እ.አ.አ መጋቢት 14 ቀን 2021 ጀምሮ የካፍ ፕሬዚዳንት ሆነው በማገልገል ላይ እንደሚገኙ ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የ60 ዓመቱ ደቡብ አፍሪካዊው ፓትሪስ ሞትሴፔ የአፍሪካ ሬንቦው ሚነራልስ ኩባንያ መስራችና ባለቤት ናቸው።

እንደ አሜሪካው የቢዝነስ መጽሔት ፎርብስ መረጃ ከሆነ÷ ፓትሪስ ሞሴፔ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ሀብት አላቸው።

ፕሬዚዳንት  ፓትሪስ ሞሴፔ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.