በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር ከ263 ሚሊየን በላይ ችግኝ ተተከለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር ከ263 ሚሊየን በላይ የችግኝ ተከላ በስኬት መጠናቀቁን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በአማራ ክልል በአንድ ቀን ጀምበር 250 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ከ263 ሚሊየን በላይ መተከሉን ነው ቢሮው የገለጸው።
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጌታቸው ጀንበር በሥነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፥ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራው አንድ አካል የሆነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የአፈር መሸርሸርን ለመከላከልና የውሃ ሃብትን ለመጠበቅ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለው በበኩላቸው ፥ ችግኝ ተከላው ለኢኮኖሚው የሚኖረውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ከግምት በማስገባት በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የቢሮው ኃላፊ “አቅደን የማናሳካው ነገር እንደሌለ የዛሬው ችግኝ ተከላ ማሳያ ነው” ያሉ ሲሆን ፥ የችግኝ ተከላው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ነው ያስታወቁት።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!