Fana: At a Speed of Life!

በቀጣይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ የህዝብ ተሳትፎና የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ ይፈጸማል – አቶ ጃንጥራር ዓባይ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ሒደት የህብረተሰቡን ተሳትፎ ባገናዘበና ተገቢነት ባለው እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ እንደሚፈፀም ሁሉም ሊገነዘበው ይጋል ሲሉ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጸሁፍ፥ በ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሐምሌ 01 ቀን 2014 እጣ አወጣጥ ላይ የተገኘውን ግኝት ተከትሎ ከተማ አስተዳደሩ የወሰደው ፈጣን እርምጃ ፍትሕን ከማሰፈን አኳያ ተገቢነት ያለው ውሳኔ ነው ብለዋል፡፡
የማጣራት ሥራው በሚመለከታቸው ተቋማት እና ከፍተኛ እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች የተከናወነ ሥራ መሆኑም የግኝቶቹን ተአማኒነት ከፍ እንደሚያደርገው ነው የገለጹት፡፡
አቶ ጃንጥራር በቀጣይ ለሚከናወኑ የእጣ አወጣጥ ሥራዎች የህብረተሰቡን ተሳትፎ ባገናዘበና ተገቢነት ባለው እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ መንገዶችን በተከተለ መንገድ እንደሚፈፀም ሁሉም ሊገነዘበው እንደሚገባ ጠቁመው÷ ለተግባራዊነቱም እንተጋለን ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.