ከተለያዩ የአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ 12 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዛሬ ጀምሮ ከተለያዩ የአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ 12 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ከተለያዩ የአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ 12 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየተሰራ አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱትም ከታንዛኒያ ፣ ማላዊ ፣ ዛምቢያ ፣ ዚምባቡዌ ፣ ጁቡቲ ፣ ሱዳን ፣ የመንና ኦማን መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በሳምንት ሶስት ጊዜ ከሪያድ እና ጂዳ ከተሞች ዜጎችን ያለ ማቋረጥ ማመላለስ መቻሉም ጠቁመው÷ ለማምጣት ከተያዘው እቅድም ግማሽ በመቶውን ማሳካት እንደታቸለም ተናግረዋል፡፡
በሁለተኛው ዙር ከኢድ እስከ ኢድ መርሐ ግብር በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንደመጡም አስረድተዋል፡፡
በተለይ ሁለተኛ ትውልድ የሚባሉት ታዳጊዎች በብዛት መምጣታቸውም ነው የተገለጸው።
በድር ኢንተርናሽናል ለ21 ዓመት ከአገር ውጭ ሲያካሂድ የቆየውን ኮንቬንሽን በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ወደ ማንነት በሚል መሪ ቃል ከነገ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሊያካሂድ እንደሆነም አምባሳደር መልስ ተናግረዋል።
በዘመን በየነ