በመዲናዋ የፈጣን አውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥባቸው መስመሮች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ ፈጣን የአውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመሥጠት ዝግጅት መጀመሩን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡
ቢሮው በመሪ ዕቅዱ የማኅበረሰቡን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ፈጣን ፣ አስተማማኝ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ተደራሽ፣ ወጪ ቆጣቢ እና አካባቢያዊ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ የብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎትና ሥርዓት መዘርጋትን ታሳቢ አድርጎ 15 የፍጥነት የትራንስፖርት ኮሪደሮችን መለየቱን አስታውቋል፡፡
በዚህም መሠረት ፈጣን የአውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት መሥመሮች እንደሚከተከለው ተለይተዋል
መሥመር-1፡- ከዊንጌት ተነስቶ በሆላንድ ኤምባሲ 3 ቁጥር ማዞሪያ አድርጎ አለርት አየር ጤና
መሥመር-2፡- ከዊንጌት በመርካቶ አድርጎ ሜክሲኮ- ጎፋ ወደ ጀሞ የሚደርስ
መሥመር-3፡- ከጉለሌ በለገሃር ጎፋ ገብርኤል አድርጎ ላፍቶ ሃና ማርያም የሚሄድ
መሥመር-4፡- ሽሮሜዳ በአራት ኪሎ በመገናኛ አድርጎ ኮተቤ ካራሎ የሚወስድ
መሥመር-5፡- ከመገናኛ በቦሌ ድልድይ አድርጎ ለገሃር
መሥመር-6፡- ከጦር ኃይሎች በቄራ አድርጎ ቦሌ ድልድይ
መሥመር-7፡- ከአየር ጤና በቶታል አድርጎ ብስራተ ገብርኤል በፑሽኪን አደባባይ ሜክሲኮ
መሥመር-8፡- ከቦሌ በኡራኤል ካዛንቺስ በአራት ኪሎ አድርጎ ስድስት ኪሎ ፈረንሳይ የሚያደርስ
መሥመር-9፡- ከአየር ጤና በመካኒሳ ቆጣሪ እስከ ቃሊቲ
መሥመር-10፡- ከቃሊቲ ቦሌ
መሥመር-11፡- ከካራሎ በሲኤምሲ ሰሚት አድርጎ በቦሌ ለሚ አይቲ ፓርክ የካ ቦሌ አራብሳ እስከ አያት
መሥመር-12፡- ከአያት በሰሚት አድርጎ ቦሌ ወረገኑ እስከ ቂሊንጦ
መሥመር-13፡- ከቡልቡላ በቂሊንጦ ኮዬ ፈጬ
መሥመር-14፡- ከለቡ በአቃቂ ኮዬ ፈጬ
መሥመር-15፡- ከኢምፔሪያል ሆቴል ጎሮ አድርጎ ቦሌ አራብሳ ናቸው፡፡
የከተማ ፈጣን አዉቶቡስ ትራንስፖርት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች እየተተገበረ ያለ ዘመናዊ የትራንስፖርት ሥርዓት ነው፡፡
ሥርዓቱ ራሱን የቻለ የተከለለ መንገድ፣ በቀላሉ የተሳፋሪን ፍሰት ማስተናገድ የሚያስችል የመጠበቂያ ቦታ ያለው መሆኑም ተገልጿል፡፡
የክፍያ ሥርዓቱም ከአውቶቡስ ውጪ የሚፈጸም ሲሆን ፣ ለአውቶቡስ ጥገናና ሥምሪት የሚያገልግል ራሱን የቻለ ዴፓ ያለው ሥርዓት ነው መባሉን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡