Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ለቀጣይ 20 ዓመታት የሚያገለግል አዲስ ክልላዊ የከተሞች ፕላን ዝግጅት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ለቀጣይ 20 ዓመታት የሚያገለግል አዲስ ክልላዊ የከተሞች ፕላን

ዝግጅት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከዩኤን ሃቢታት ጋር በመተባበር በአማራ ክልል በሚተገበረው አዲስ ፕላን ላይ ውይይት እያካሄደ ነው።

በመድረኩ አዲሱ የከተመሞች ፕላን በሌሎች ክልሎች ቀድሞ እንደተጀመረ የተገለጸ ሲሆን ÷በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ዘግይቶ አሁን ላይ ወደ ተግባር ምዕራፍ ለመግባት በክልሉ ከተለያዩ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ከተውጣጡ የሥራ ኀላፊዎች ጋር እየተመከረበት ነው ተብሏል።

በእቅድ ውይይቱ ላይ የተገኙት በከተማና መሠረተ ልማትሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ደጀን በአማራ ክልል ብቻ ከ600 በላይ ከተሞች መኖራቸውን ጠቁመው÷ እነዚህን ከተሞች ያለ ፕላን መምራት አስቸጋሪ በመሆኑ ፕላን ማዘጋጀት አስፈልጓል ብለዋል፡፡

የከተሞችን ዘርፈ ብዙ እድገትና ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ አዲስ እቅድ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ በሀገር አቀፍ ደረጃም ዝግጅቱ ተጠናቆ ወደ ስራ ተገብቷል ነው ያሉት።

የአማራ ክልል መንግስት የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው÷ የሚዘጋጀው ፕላን የከተማና ገጠር ግንኙነትን ጤናማ ለማድረግና የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማፋጠን የሚያስችል ነው ብለዋል።

ይህ ፕላን ተዘጋጅቶ ሲጠናቀቅም ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች ተቀናጅተው እንዲሰሩ እና አዲሱ ፕላን በፍጥነት ተዘጋጅቶ ወደ ስራ እንዲገባ ጥረት ይደረጋልም ነው የተባለው፡፡

በሙሉጌታ ደሴ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.