በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ ወጣቶች የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ወጣቶች ለሰላም ግንባታና አካባቢ ጥበቃ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የአፍሪካ 2022 የወጣቶች የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ፡፡
የምክክር መድረኩ መጠናቀቅን ተከትሎም ተሳታፊዎች በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተገኘተው ችግኝ በመተከል አርንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አመራሮች፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥት ተወካዮች፣ የሲቪክ ማህበራት ተጠሪዎች ወጣቶች የስካውት አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል::
የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ዳይሬክተር ካቢሳ ዶሚቲየን ÷ ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ የሰላም ግንባታና የአከባቢ የአየር ንብረት ጥበቃ እጅግ አሰፋለጊና ወቅታዊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስትም የአርንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን ሀገራዊ አጀንዳ አድርጎ እየተገበረው በመሆኑ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል ፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው÷ ዛሬ የተከናወነው የአርንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአፍሪካውያን መካከል የተፈጠረውን አብሮነትና ወንድማማችነት የሚያጠናክር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ከዚህ ባለፈም መርሐ ግብሩ በአከባቢ ጥበቃና በሰላም ግንባታ ሂደት ወጣቶች ጉልህ ሚና እንዳላቸው የሚያሳይ ነው::