Fana: At a Speed of Life!

አቶ ምትኩ ካሳ ፍርድ ቤት ቀረቡ

 

አዲስ አበባ፣  ሐምሌ 7፣  2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ትናንት በቁጥጥር ስር የዋሉት የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር የቀድሞው ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

አቶ ምትኩ ካሳ እና ኢያሱ ምትኩ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።

ፖሊሰ በተጠርጣሪዎቹ ላይ እስካሁን ያሰባሰባቸውን መረጃዎች እና ማስረጃዎች ለፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡

የ10 ምስክሮችን ቃል ለመቀበል እንዲሁም በፌደራል እና በክልሎች በሚገኙ የኮሚሽኑ ቅርንጫፎች ያሉ ሰነዶች ኦዲት ለማድረግ እንዲሁም በብርበራ የተገኙ ሰነዶች እና ምንጩ ያልታወቀ የውጭ ሀገር ገንዘብን ለማጣራት እና ምርመራ ለማድረግ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቅዶለታል፡፡

ተጠርጣሪዎች በጠበቆቻቸው አማካኝነት በጉዳዩ ላይ የቀድሞ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና ፖሊስ የምርመራ ጊዜ ከአንድ ዓመት በፊት ያለቀ በመሆኑ ለፖሊስ እንዳይሰጥ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ግራ ቀኙን የተመለከተው ችሎቱ ለፖሊስ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜን የፈቀደ ሲሆን፥ ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄን ውድቅ አድርጓል።

በበላይ ተስፋዬ

አቶ ምትኩ ካሳ የተጠረጠሩበትን የሙስና ወንጀል ዝርዝር ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ https://www.fanabc.com/የብሔራዊ-አደጋ-ስጋት-ስራ-አመራር-ኮሚሽን/

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.