ሊጉ ከ10 ሺህ በላይ መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አበረከተ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ 10 ሺህ 653 መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አበርክቷል፡፡
መጻሕፍቱን የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ኃላፊ የሺ ወልዴ ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የበላይ ጠባቂ ኢንጅነር ውባየሁ ማሞ ማስረከባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የሺ ወልዴ እንደገለጹት÷ መጻሕፍቱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና በስራቸው ባሉ የወረዳ የአዲስ አበባ ብልጽግና ሴቶች ሊግ አባላት የተሰበሰቡ ናቸው፡፡
መጻሕፍቱን የተረከቡት የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የበላይ ጠባቂ ኢንጅነር ውባየሁ ማሞ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!