Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪም ይሁን ወራሪ ኃይልን ለመደምሰስ በአስተማማኝ ወታደራዊ ቁመና ላይ እንገኛለን – ሜጄር ጀኔራል ናስር አባዲጋ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በሚሰጠን ትዕዛዝ መሰረት አሸባሪም ይሁን ወራሪ ኃይልን ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ በአስተማማኝ ወታደራዊ ቁመና ላይ እንገኛለን ሲሉ ሜጄር ጀኔራል ናስር አባዲጋ ገለጹ፡፡

በደቡብ ዕዝ የሚገኘው የሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ከየትኛውም አቅጣጫ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ለመመከት በሚያስችል የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

የሜካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ሜጄር ጀኔራል ናስር አባዲጋ እንደተናገሩት፥ በየትኛውም ጊዜና ሰዓት መንግስት በሚሰጠን ትዕዛዝ መሰረት አሸባሪም ይሁን ወራሪ ኃይልን ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ በአስተማማኝ ወታደራዊ ቁመና ላይ እንገኛለን።

ዋና አዛዡ አክለውም ፥ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ለእግረኛ ኃይላችን የተኩስ ድጋፍ ለመስጠትና በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁነቱን አረጋግጧል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.