Fana: At a Speed of Life!

ሀገራችን ለጀመረችው የዕድገት ጉዞ የሚጠበቅብንን አስተዋፅኦ በማበርከት  የተከበረች ኢትዮጵያን ለትውልድ እናስረክባለን- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታችንን እውን ከማድረግ ባለፈ ሀገራችን ለጀመረችው የዕድገት ጉዞ ከእኛ የሚጠበቀውን ሁሉ አስተዋፅኦ በማበርከት የበለፀገችና የተከበረች ኢትዮጵያን ለተተኪው ትውልድ እናስረክባለን ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ፡፡

የመከላከያ መሬት ይዞታና ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአዲስ አበባ ራሽያ ካምፕ ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ ያስገነባውን 17 ክፍሎች ያሉትን የሠራዊት መኖሪያ ቤት በ100 ቀናት ውስጥ ገንብቶ በማጠናቀቅ አስመርቋል፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ቤቶቹን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የዘመናዊ ሰራዊት ግንባታችንን እውን ከማድረግ ባለፈ ሀገራችን ለጀመረችው የእድገት ጉዞ እንደተቋም ከእኛ የሚጠበቀውን ሁሉ አስተዋፅኦ በማበርከት የበለፀገችና የተከበረች ኢትዮጲያን ለተተኪው ትውልድ ለማስረከብ ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

ሰራዊታችን ባለፉት ሁለት ዓመታት በከባድ ሀገራዊ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ በአንድ በኩል ሀገሩን ከፀረ ሰላም ኃይሎች እኩይ ሴራና ድርጊት እየጠበቀና እየተከላከለ÷ በሌላ መልኩ ደግሞ በርካታ የሰራዊቱን ወትሮ ዝግጁነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን በስፋት፣ በጥራትና በፍጥነት መስራት ችሏል ብለዋል፡፡ ይህ ፕሮጀክትም የዚሁ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዳይሬክቶሬቱ አባላት የተሰጣቸውን ተልዕኮ ተቀብለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥራት ያለው ስራ ሰርተው ለምረቃ በማብቃታችውም አመስግነዋል፡፡

እስካሁን በተሠሩ ዘርፈ ብዙ ውጤታማ ተቋማዊ የግንባታ ስራዎች ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ ፍጥነትና ጥራት ሰራዊቱን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል፡፡

በዳይሬክቶሬቱ የተዘጋጀውን የማበረታቻ ሽልማትና የእውቅና የምስክር ወረቀት በግንባታው የላቀ አስተዋፅኦ ለነበራቸው አባላት ማበርከታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.