Fana: At a Speed of Life!

የኢኮኖሚው ዘርፍ በበርካታ ችግሮች ውስጥ ቢሆንም አበረታች ስኬት አስመዝግቧል አሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኮኖሚው ዘርፍ በበርካታ ችግሮች ውስጥ ሆኖ አበረታች ስኬት ማስመዝገቡን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለጹ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮችና ሥራ አስፈጻሚዎች በወቅታዊ ጉዳይ፣ ባለፉት ዓመታት ስለታዩ ለውጦችና ስለገጠሙ ፈተናዎች እንዲሁም በቀጣይ መከናወን ስለሚገባቸው ሥራዎች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል÷ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲው ዘርፎች እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን አንስተዋል፡፡

በተለይ የኢኮኖሚው ዘርፍ በበርካታ ችግሮች ውስጥ ሆኖ አበረታች ስኬት እንዳስመዘገበ ጠቅሰው÷ በወጪ ንግድ ዘርፍ ካለፉት ዓመታት የተሻለ ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል፡፡

የተጀመሩ አገራዊ ፕሮጀክቶች የተለያዩ የምዝበራ ችግሮች የነበሩባቸው ቢሆንም፥ በተቀናጀ የፕሮጀክት አመራር ሊጠናቀቁ መቻላቸውን እና የብድር ዕዳ ጫና ለመቀነስ እየተሰራ ያለውን ስራ ማብራራታቸውንም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.