የሀገር ውስጥ ዜና

በ2014 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 12 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኘ

By Meseret Awoke

July 15, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 12 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱን የንግድን ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በበጀት ዓመቱ ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 63 ቢሊየን የአሜሪካን ለማግኘት አቅዶ ነው 4 ነጥብ 12 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉ ተገልጿል፡፡

አፈጻጸሙ ባለፈው በጀት ዓመት ከተገኘው 3 ነጥብ 62 ቢሊየን ዶላር የ13 ነጥብ 81 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

አጠቃላይ ከተያዘው የወጪ ንግድ ገቢ እቅድ አንፃር የግብርናው ዘርፍ 72 በመቶ ገቢ በማስገኘት ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ ሲሆን ፥ ማዕድን 14 በመቶ፣ ኢንዱስትሪ 12 በመቶ እንዲሁም ኤሌክትሪክ ሁለት በመቶ ገቢ ማስገኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!