የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል በሚሊየን ለሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እህል ማቅረብ በመቻሉ  ሊያጋጥም የነበረ የረሃብ አደጋ መቀልበሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለፀ

By Mekoya Hailemariam

July 16, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  በትግራይ ክልል በሚሊየን ለሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እህል ማቅረብ በመቻሉ ሊያጋጥም ይችል የነበረን የረሃብ አደጋ መቀልበሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለፀ።

የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቢሮው የሰሜን ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አድሪያን ቫን ደር ክናፕ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ  እንደተናገሩት፥ መንግስት ለሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ለማሳለጥ ግጭት ለማቆም በመወሰኑ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሚሊየን ለሚቆጠሩ ዜጎች የምግብ እህል ማድረስ ችሏል።

የግጭት ማቆም ውሳኔውን ተከትሎ በመቶ የሚቆጠሩ ተሽከርካሪዎች ምግብ በመጫን በክልል እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ማድረስ ችለዋል።

ከግጭት የማቆም ውሳኔው በኋላ ያለማቋረጥ የምግብ አቅርቦት እየተካሄደ መሆኑን በማንሳትም እስካሁን 4 ሺህ ተሽከርካሪዎች እህል ወደ ትግራይ ክልል ማስገባታቸውን ገልፀዋል።

በዚህም ምክንያት ለ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች ምግብ ማቅረብ ተችሏል።

ሆኖም ግጭቱ በጎዳቸው የአማራ እና አፋር አካባቢዎች መድረስ ይጠበቅብናል ያሉት ሀላፊው፥ ይህን ለማድረግ የግጭት ማቆም ውሳኔው ተግባራዊነት መቀጠል ይገባዋል፤ ተጨማሪ የፋይናንስ ድጋፍም ያስፈልገናል ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-