ልጆችና ችግኝ አንድ ናቸው ሁለቱም እንክብካቤን ይሻሉ – ዶክተር ለገሰ ቱሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ልጆችና ችግኝ አንድ ናቸው ሁለቱም እንክብካቤን ይሻሉ ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለጹ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤትና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ባለሙያዎች በምዕራብ አርሲ ዞን ሻላ ወረዳ ተገኝተው ችግኝ ተክለዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ የተገኙት ዶክተር ለገሰ ቱሉ፥ በሻላ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራቸውን ያሳረፉ ሲሆን፥ “ልጆችና ችግኝ አንድ ናቸው ሁለቱም ክብካቤን ይሻሉ” ሲሉ ህብረተሰቡ በዘመቻው የተከለውን ችግኝ እንዲንከባከብ አሳስበዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪ ቀን በቀን ችግኝ መትከልን የእለት ተዕለት ተግባርና መዝናኛው ማድረግ እንዳለበት ጠቅሰው÷ የተተከሉ ችግኞች መንከባከብና ከፍሬው ማድረስም አለበት ነው ያሉት፡፡
የምዕራብ አርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሀጂ በበኩላቸው፥ አከባቢው በዞኑ በተደጋጋሚ ድርቅ ከሚያጥማቸው ወረዳዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፥ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ችግኝ በመትከል የድርቅ ሁኔታን መቀየር ይገባል ብለዋ፡፡
በተጨማሪም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትና ተጠሪ ተቋማት በሲራሮና ሻላ ወረዳዎች ከትምህርት ገበታ እየተስተጓጎሉ ላሉ 11 ሺህ ተማሪዎች 7 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ አበርክተዋ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትና 16 ተጠሪ ተቋማት በትናንትናው እለት በሻሸመኔ ከተማ የ35 አቅመ-ደካሞችን ቤት የማደስ መርሐ ግብር ማስጀመራቸው ይታወሳል፡፡
በጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!