Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ከ20 ላይ ይካሄዳል፡፡

በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው እና ሁለተኛ ቀኑን በያዘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና÷ ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ታካሂዳለች፡፡

በፍጻሜ ውድድሩም አትሌት ቦስና ሙላቴ፣  አትሌት እጅጋየሁ ታየ እና አትሌት ለተሰንበት ግደይ እንደሚሳተፉ የወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል ምሽት 5 ሰዓት ከ 5 ላይ በሚካሄድ የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ እና አትሌት ፍሬ ወይኒ ኃይሉ ይሳተፋሉ፡፡

እንዲሁም ምሽት 2 ሰዓት ከ35 ላይ በሚካሄደው የሴቶች 3ሺህ ሜትር የመሰናክል ማጣሪያ÷ አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ፣ አትሌት መቅደስ አበበ እና አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው እንደሚሳተፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ መርሐ ግር ደግሞ ሌሊት 10 ሰዓት ከ30 ላይ የወንዶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ የሚካሄድ ሲሆን÷ አትሌት ሳሙኤል አባተ፣ አትሌት ሳሙኤል ተፈራ እና አትሌት ታደሰ ለሚ ይሳተፋሉ፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.