Fana: At a Speed of Life!

በቦሌ ክፍለ ከተማ የጦር መሳሪያ እና በህገ ወጥ መንገድ የተከማቸ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና በህገ ወጥ መንገድ የተከማቸ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለፀው ፥ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በክፍለ ከተማው ወረዳ 12 ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እንደሚገኝ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ የህግ አግባብን ተከትሎ በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት ብርበራ አድርጓል፡፡

በወቅቱ በተደረገው ብርበራም አንድ ሽጉጥ ከመሰል 91 ጥይት ጋርና በህገ ወጥ መንገድ የተከማቸ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከካዝና ውስጥ ተይዞ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ከከተማው ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለከታል፡፡

በመዲናዋ አስተማማኝ ሰላም እንዲኖርና ሁከትና ሽብር ለመፍጠር የሚያስቡ አካላት ምኞታቸው እንደማይሳካ የሚያረጋግጥ ተግባራዊ ምላሽ እየሰጠ የሚገኘው የከተማው ነዋሪ አሁንም ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ለአካባቢው ሰላም ዘብ መቆሙንና መረጃ እና ጥቆማ መስጠቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.