ስፓርት

በኦሬገን ዛሬ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች ማራቶንና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ይጠበቃሉ

By Mekoya Hailemariam

July 17, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶች ማራቶን እና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች ይጠበቃሉ።

ቀን 10 ሰዓት ከ15 ላይ የወንዶች ማራቶን የሚካሄድ ሲሆን፥ ሌሊሳ ደሲሳ፣ ሙስነት ገረመው፣ ሰይፉ ቱራ እና ዓየለ ቶላ ይሮጣሉ።

ምሽት 5 ሰዓት ላይም የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ይካሄዳል።

በዚህ ሩጫ በሪሁ አረጋዊ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ታደሰ ወርቁ ይሮጣሉ።