Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ1ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 67 ድልድዮች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2014 በጀት ዓመት ከ1ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 67 ድልድዮች ግንባታቸው ተጠናቆ ተመርቀዋል፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተሞች ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት÷በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለህዝብ ቅሬታ ምንጭ የነበሩ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ወንዞች ላይ ድልድዮችን የመገንባት ስራ ተከናውኗል፡፡
በዚህም በ2014 በጀት ዓመት በ1ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 67 ድልድዮች ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ጠቁመዋል፡፡
በእነዚህ በተለያዩ ወንዞች ላይ በተሰሩ ድልድዮችም 272 የሚሆኑ የገጠር ቀበሌዎችን ማስተሳሰር መቻሉን አመላክተዋል፡፡
በቀጣይም የህዝቦችን የመልካም አስተዳደር ችግር በዘላቂት ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ነው ያሉት፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.