Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል የ2014/15 የመኸር ግብርና የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የ2014/15 በጀት ዓመት የመኸር ግብርና የንቅናቄ መድረክ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ዱራሜ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
 
የንቅናቄ መድረኩ “በበጋ መስኖ የጀመርነውን የተቀናጀ ጥረት በመኸር ግብርናም እንደግመዋለን!” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው።
 
በመርሐ ግብሩ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳ፣ በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንዱሁም ሌሎች የክልሉ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ የመኸር እርሻ 1 ሚሊየን 454 ሺ ሄክታር መሬትን በተለያዩ ሰብሎች በመሸፈን ከ99 ሚሊየን በላይ ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተመላክቷል፡፡
 
በ2014/15 በልግ ወቅት 992 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በማልማት ከ 83 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት መታቀዱ ነው የተገለጸው፡፡
 
በዚሁ ምርት ዘመን ከ 148 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ ላይ የተዘራው ምርት በተባይና በዝናብ መቆራረጥ ምክንያት ለጉዳት መዳረጉ የተገለጸ ሲሆን÷ይህንን ለማካካስ የመኸር ወቅቱን አጠናክሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡
 
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርዕስቱ ይርዳ ግብርናን በማዘመን የምግብና የስነ-ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንተጋለን ብለዋል።
 
ርዕሰ መስተዳድሩ ለመኸር እርሻ ትኩረት እንስጥ ሲባል የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለማቃለል አቅርቦትን በማሻሻል ምርታማነትን ማሳደግ እንዲሁም በልግ ላይ የታጣውን ምርት መኸር ላይ በማካካስ የሕዝቡን ኑሮ ማሻሻል ሲቻል ነው ብለዋልል፡፡
 
በማቴዎስ ፈለቀ እና መለሰ ታደለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.