Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በቢሾፍቱ የከተማ ግብርና ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ መንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በቢሾፍቱ ከተማ ተገኝተው የከተማ ግብርና ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር÷ የክልሉ መንግስት በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ጠቅሰው፥ እነሱም በከተማ ግብርና እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ፣ ፣ የፈጠራና ክህሎትን ማበረታታት እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍን መማፋን መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም ÷ በአዲስ ጉልበት ለከተማ ግብርና ትኩረት በመስጠት የብልጽግና ጉዟችንን እናረጋግጣለንም ነው ያሉት፡፡

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ልዑክ በቢሾፍቱ ከተማ በነበረው ቆይታ የከተማ የዶሮ እርባታ፣ የወተት ከብቶችንና የአሳማ እርባታ ፣ የንብ ማነብ እና የማር ምርት፣ የአትክልት ማዳበሪያ ዝግጅት ስራዎችን መጎብኘቱም ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.