Fana: At a Speed of Life!

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሦስት የፍጻሜ ውድድሮች ትሳተፋለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ የሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ኢትዮጵያ በሦስት የፍጻሜ ውድድሮች ትሳተፋለች፡፡

በዚህም መሰረት ቀን 10:15 በሚካሄደው የሴቶች ማራቶን ፍጻሜ ጎይቲቶም ገብረስላሴ፣ አባበል የሻነህ እና አሸቴ በከሪ ይሳተፋሉ፡፡

ሌሊት 11፡20 በሚካሄደው የወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ፍጻሜ ውድድር ደግሞ፣ ሃይለማርያም አማረ፣ ጌትነት ዋለ እና ለሜቻ ግርማ የሚሳተፉ ይሆናል።

በተጨማሪም ሌሊት 11:50 በሚደረገው የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍጻሜ ውድድር ሂሩት መሸሻ፣ ጉዳፍ ጸጋዬ እና ፍሬወይኒ ሃይሉ ሀገራቸውን ይወክላሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ሌሊት በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ የወንዶች ውድድር ታደሰ ለሚ 3:35 በመግባት ከምድብ ሁለት ማለፍ ሲችል ሳሙኤል ተፈራ 9ኛ ደረጃ በመውጣቱ ከምድቡ ሳያልፍ መቅረቱን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.