Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በሁለት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን መርምሮ እንዲጸድቁ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም በግብርና፤ በማምረቻው ዘርፍ እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች በ47 ፕሮጀክቶች ላይ በመምከር ነው ውሳኔ ያሳለፈው።

ፕሮጀክቶቹ ካላቸው ጠቀሜታ አንጻር በተለይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ የቀረቡት ፕሮጀክቶች ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል እንደሚፈጥሩ ታምኖባቸው በልዩ ትኩረት ይሰራሉ ተብሏል።

በክልሉ መዋዕለ ንዋያቸውን ለሚያፈሱ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ዘርፉን ማበረታታት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም ምክር ቤቱ በዝርዝር ተመልክቷል።

ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ የክልሉን ስፖርት ምክር ቤት ለማቋቋም የቀረበውን ደንብ ማጽደቁን ከደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.