Fana: At a Speed of Life!

እስከ ትናንት ድረስ 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኝ ተተክሏል – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአጠቃላይ እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በተደረገው ርብርብ እንደ ሀገር ከ4 ነጥብ 2 ቢሊየን በላይ ችግኝ መተከሉን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
“ዐሻራችን ለትውልዳችን” በሚል መሪ ቃል እየተተከለ ያለው የ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር÷ በአማራ ክልል በተደረገው ተከላ 263 ነጥብ 15 ሚሊየን፣ በኦሮሚያ ክልል 469 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች መተከላቸውን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ ደቡብ ክልል በአንድ ጀምበር 100 ሚሊየን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል መታቀዱ ተመላክቷል፡፡
በአጠቃላይ እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም በተደረገው ርብርብ እንደሀገር ከ4 ነጥብ 2 ቢሊየን በላይ ችግኝ መተከሉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.