የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አፍሪካውያን ስደተኞች የተሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተጀመረ

By Meseret Awoke

July 19, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የስደተኞች መጠለያ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ስደተኞች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተጀመረ።

ስደተኞች የሚሳተፉበት መርሐ ግብር ጾሬ፣ ባምባሲና ሸርቆሌ የመጠለያ ካምፖች እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በካምፖቹ በዘንድሮው ክረምት 200 ሺህ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የአሶሳ ቅርንጫፍ ሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ፕሮግራም ኃላፊ አቶ ፍሬዘር ፈለቀ ለኢዜአ ገልጸዋል።

በጾሬ፣ ባምቢስና ሸርቆሌ የስደተኞች መጠለያ ካምፓች ከሱዳን፣ ደቡቡ ሱዳን፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ርዋንዳና ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የመጡ ከ74 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ ከስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!