አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በሚቀጥለው በጀት ዓመት የተልዕኮየን 60 በመቶ እፈጽማለሁ አለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በ2015 በጀት ዓመት 60 በመቶ ተልዕኮውን እንደሚፈጽም አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ከሦስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱ ላይ የ2015 በጀት ገቢራዊ እቅዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተባባሪና አማካሪ ኮሚቴ አቅርቧል፡፡
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው ፥ በትግበራ ምዕራፍ 20 ሺህ መድረኮች በማዘጋጀት ሁለት ሚሊየን ሰዎች እናወያያለን ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከ3 ነጥብ 2 ቢለየን በላይ ብር ከመንግስት የሚጠይቅ ሲሆን ፥ 208 ሚሊየን ብሩ ከአጋር ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡
አጀንዳ ና ተሳታፊ ልየታ፣ መዋቅር ዝርጋታና መሰል ተግባራት የቀጣይ ተግባራት አቅጣጫዎች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡
በኃይለየሱስ ስዩም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!