ፋና ስብስብ

በኡጋንዳ ሃሰተኛ የኮሮና ቫይረስ ክትባት የሰጡ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Feven Bishaw

March 11, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በኡጋንዳ ሃሰተኛ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሰጥተዋል የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ክትባቱ በአፍ የሚወሰድ ፈሳሽ ሲሆን፥ ፖሊስ የፈሳሹን ናሙና በመውሰድ ምርመራ መጀመሩ ተመላክቷል።

ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች ከካምፓላ 120 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኘው ማዩጌ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ግለሰቦቹ ክትባቱን የሰጡት በነፃ ሲሆን፥ ምን ያክል ሰው ክትባቱን እንደወሰደ ግን የታወቀ ነገር የለም ፡፡

ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት እስካሁን 18 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ዓለም ላይ ከ90 በላይ ሀገራትን ያዳረሰ ሲሆን፥ 3 ሺህ 800 የሚሆኑ ሰዎችንም ለህልፈት ዳርጓል።

የህክም ባለሙያዎችም ለቫይረሱ መድሃኒት ለማግኘት እየሰሩ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ እስካሁን ቫይረሱን ሊያክም የሚችል ክትባት አልተገኘም።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision