Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ጋር ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ጃፓን መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት እና ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በሀገራቱ መካከል ባለው የኢንቨስትመንት ግንኙነት፣ ሰብዓዊ እርዳታ እና በሌሎች ዘርፎች ለይ በትኩረት መወያየታቸውን በኢትዮጵያ ከጃፓን ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በምክክሩ ጃፓን እስካሁን በኢትዮጵያ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የ23 ሚሊየን ዶላር ሰብዓዊ እርዳታ ማድረጓ ተጠቁሟል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.