Fana: At a Speed of Life!

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ተቋማት ግንባታን ለማስጀመር ሰመራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአሸባሪው ህወሃት ወረራ የወደሙ የትምህርት ተቋማት ግንባታን ለማስጀመር ሰመራ ገብተዋል፡፡
ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት ሰመራ ከተማ በሚገኘው ሱልጣን አሊ ሚራህ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
ሚኒስትሩ በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ በተመረጡ አካባቢዎች አሸባሪው ህወሃት ወረራ ፈጽሞ በነበረበት ወቅት የወደሙ የትምህርት ተቋማትን የመልሶ ግንባታ መርሃ ግብር ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በይፋ ያስጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።
ሚኒስቴሩ ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት እስከ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ድረስ ግብረ-ህይል አቋቁሞ የተለያዩ ስራዎችን መስራቱ ይታወቃል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.