Fana: At a Speed of Life!

ኢራን እና ሩሲያ በቀጠናው ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በቴህራን ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የሀገራቱን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከርና በቀጠናው ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ትብብር ለማሳደግ ተስማምተዋል።

ሽብርተኝነትን በመዋጋት የተመዘገቡትን የጋራ ድሎች ያወደሱት ራይሲ እና ፑቲን በቀጠናው ያለውን ትብብር ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሶሪያ ውስጥ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚደረገው የሁለትዮሽ ትብብር ላይ የኢራኑ ፕሬዚዳንት መሰል ትብብሮች የአካባቢውን ደህንነት እና መረጋጋትን ለማስፈን ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን በበኩላቸው ሩሲያ እና ኢራን በተለይም በዓለም አቀፍ ደህንነት ያላቸው ትብብር መጨመሩን አንስተዋል።

በሶሪያ ያለውን ቀውስ ለመፍታት በሚደረገው ጥረትም ሁለቱ ወገኖች ትልቅ ድርሻ አላቸው ማለታቸውን ሺንዋ ዘግቧል።

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.