Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ታከለ በከተማ ግብርና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በከተማ ግብርና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በዚህ ወቅትም የከተማ አስተዳደሩ በዘርፉ የተሰማሩ አካላትን ከመደገፍ ጎን ለጎን ሌሎች ተጨማሪ ወጣቶችን በማህበር በማደራጀት ገቢ እንዲያገኙ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በዘርፉ ላይ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍም የከተማ ግብርናን በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት ከተማዋ የያዘችውን የአረንጓዴ ልማት ከግብ ለማድረስ ይሰራል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የከተማ አስተዳደሩ በአዲስ አበባ የከተማ ግብርናን በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት ለነዋሪዎች ተጨማሪ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በከተማዋ ውስጥ የከብት እርባታን ጨምሮ በፍራፍሬ ምርት፣ ንብ ማነብ እንዲሁም አትክልትን በማምረት ስራ ላይ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወጣቶችን እና እናቶችን አደራጅቶ ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።

የከተማው የወንዝ ዳርቻ ልማት አካል የሆነው የከተማ ግብርና፥ የተጎዳ አካባቢን መልሶ እንዲያገግም ለማድረግ ያግዛል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ነዋሪው የራስ የምግብ ፍጆታን በመሸፈን ቀሪውን ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ አስችሏል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.