የአሜሪካው ስታርኪይ ሂሪንግ ፋውንዴሽን የመስማት ችግር ላለባቸው ሰዎች የማዳመጫ መሳሪያ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ስታርኪይ ሂሪንግ ፋውንዴሽን የተሰኘው የአሜሪካ ግብረ ሰናይ ድርጅት የመስማት ችግር ላለባቸው ሰዎች የማዳመጫ መሳሪያ ድጋፍ አደረገ።
መሳሪያው ድርጅቱ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያደረገው ድጋፍ ነው።
ድጋፉ በጅማ እና አካባቢው ለሚገኙና የመስማት ችግር ላለባቸው 1 ሺህ ሰዎች የተደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ የድርጅቱ ተወካይ ዶክተር ጣዕመ አምባዬ ተናግረዋል።
ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በአክሱም፣ መቐለ፣ አዲስ አበባ እና አርባ ምንጭ ለ9 ሺህ 47 ሰዎች ድጋፍ ማድረጉንም አስታውሰዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የጅማ ዩኒቨርሲቲ እና ከካተራክት ቪዥን ኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የአይን ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል።
በዚህ ነጻ አገልግሎትም 500 የሚሆኑ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል።
በአብዱራህማን መሃመድ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision