Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ፍፃሜ በሁለት አትሌቶች ትወከላለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከንጋቱ 11 ሰዓት ከ45 ላይ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል፡፡
በፍጻሜው መቅደስ አበበ እና ወርቅውሃ ጌታቸው ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።
በሌላ በኩል ከሌሊቱ 8 ሰዓት ከ25 ላይ የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች የማጣሪያ ውድድር የሚካሄድ ሲሆን÷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ፣ ጉዳፍ ፀጋይ እና ዳዊት ስዩም ይሳተፋሉ፡፡
በሌላ መርሐ ግብር ደግሞ ሌሊት 9 ሰዓት ከ20 በሚካሄደው የ800 ሜትር የወንዶች ማጣሪያ ውድድር ኤርሚያስ ግርማ እና ቶሎሳ ቦደና ይሳተፋሉ፡፡
በአሜሪካ ኦሬገን እየተካሄደ የሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
በደረጃ ሰንጠረዡም÷ ኢትዮጵያ 3 የወርቅ እና 3 የብር በአጠቃላይ በ6 ሜዳሊያዎች ከአሜሪካ በመቀጠል 2ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.