Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ሃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ሃላፊ ጆን ሮቢንሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በምክክሩ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና በአሜሪካ መንግስት መካከል ስላለው ኢኮኖሚያዊ አጋርነት ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም ከአጎዋ መቀጠል ጋር ተያይዞ የአሜሪካን ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች እና ስትራቴጅዎች ላይም ተወያይተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲም የግሉን ዘርፍ ተሳታፊነት በማሳደግ እና የኢንቨስትመንት ከባቢውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጡን ከኢንቨስትመንት ከሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.