ስፓርት

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ለፍጻሜ አለፉ

By Mekoya Hailemariam

July 21, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜው ውድድር አለፉ።

በርቀቱ ኢትዮጵያን ወክለው ከተካፈሉት አትሌቶች ለተሰንበት ግደይ፣ ጉዳፍ ፀጋይ እና ዳዊት ስዩም ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል በወንዶች 800 ሜትር ማጣሪያ ቶለሳ ቦደና ወደ ቀጣይ ዙር አልፏል።