Fana: At a Speed of Life!

ጨፌ ኦሮሚያ 158 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበውን የክልሉ መንግስት የ2015 በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ 158 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበውን የክልሉ መንግስት የ2015 በጀት አጸደቀ።

ጨፌው ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ፥ ለክልሉ መንግስት 158 ቢሊየን 629 ሚሊየን 503 ሺህ 205 ብር የ2015 በጀት ማጽደቁን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ጨፌ ኦሮሚያ ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ በቆየው ጉባዔ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡

በዚህም፥ ኮሚሽነር ከፋለው ተፈራ የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አዲሱ አረጋ የኦ ቢ ኤን ቦርድ ሰብሳቢ እና አቶ ሞገስ ኢደኤ ደግሞ የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

በተጨማሪም በየደረጃው ለሚገኙ ፍርድ ቤቶች የ320 ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.