Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በአንድ ጀምበር ከ7 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አረንጓዴ ዐሻራ የማኖር የክረምት መርሐ ግብር ላይ በአንድ ጀምበር ከ7 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የክልሉ ግብርና እና ተፈጥሮ ሐብት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው የተፈጥሮ ሐብት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ በቀለ አንበሳ በሰጡት መግለጫ ÷ በክልሉ በዛሬው ዕለት ብቻ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 7 ሚሊየን 768 ሺህ 991 ችግኞችን በመትከል ከዕቅድ በላይ ማሳካት ተችሏል ብለዋል፡፡

የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላው መርሐ ግብር በ7 ሺህ 200 ሄክታር መሬት ላይ መከናወኑን የገለጹት ምክትል ኃላፊው ÷ በአረንጓዴ ዐሻራ 174 ሺህ 390 የኅብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ጠቁመዋል።

አቶ በቀለ፣ በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ላይ ለተሳተፉ አካላት ሁሉ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

በዛሬው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ የታየውን ተሳትፎ በማጠናከር በቀጣይም በክልሉ በ4ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የተያዘውን ከ45 ሚሊየን በላይ ችግኝ ተከላ ለማሳካት ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በችግኝ ተከላው ላይ እየተደረገ ያለውን ተሳትፎ በመንከባከቡ ላይ ማጠናከር እንደሚገባም ምክትል ኃላፊው መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.